ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ከርዋንዳው ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከርዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ጋር በዛሬው ዕለት ተወያዩ።
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በዛሬው ዕለት ወደ ርዋንዳ ኪጋሊ አቅንተዋል።
በቆይታቸውም ከፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ጋር በሁለት ሀገራት ግንኙት ዙሪያ መምከራቸውን ከርዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ይፋዊ የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ከዚህ ቀደም ከኬንያው ፕሬዚዳንት አሁሩ ኬንያታ እና ከኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ጋር መወያየታቸው የሚታውስ ነው።
በወቅቱም በሀገራቱ ግንኙነት እንዲሁም በህዳሴ ግድብ ዙሪያ እየተካሄደ በሚገኘው ውይይት ላይ በማተኮር ተወያይተዋል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision