Fana: At a Speed of Life!

25 ተቋማት በ“ኦንላይን” አገልግሎት እየሰጡ ነው

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 25 ተቋማት 326 የአገልግሎት ዘርፎችን በ“ኦንላይን” እየሰጡ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  አስታወቀ፡፡

በሚኒስቴሩ የኤሌክትሮኒክስ አገልግሎት ካለማላቸው ተቋማት ጋር የ”አገልግሎት ቀን” አከባበርን በማስመልከት ተወያይቷል።

የተቋማቱ ኃላፊዎች በ“ኦንላይን” የሚሰጧቸውን አገልግሎቶች በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ÷ በ”አገልጋይነት ቀን” ወደ ተገልጋዮቻቸው ወርደው አገልግሎቶቻቸውን እንደሚሰጡ ገልጸዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ እንደገለጹት ÷ ”የ”አገልጋይነት ቀን” በኤሌክትሮኒክስ አገልግሎት ሁሉንም ዜጎች በእኩልነት ተደራሽ ለማድረግ የሚሰራ ፕላትፎርም ነው፡፡

በቀጣይ አገልግሎት ፈላጊ ዜጎች ወደ ተቋማት መሄድ ሳያስፈልጋቸው የክፍያ ስርዓቱን በማጣመር የአገልግሎቱን ውጤት ባሉበት ለማስረከብ እየተሠራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ተገልጋዮች በ”ኦንላይን” ከመጠቀም ይልቅ በአካል ይዘው የመምጣት ልማድ እንዳለባቸው እንደክፍተት ተነስቷል።

የተቋማቱ ኃላፊዎች በ”አገልጋይነት ቀን” በኦንላይን አመልክተው አገልግሎት የጠየቁ ደንበኞችን ጉዳይ ጨርሰው ባለቡት በማድረስ ያገለግላሉ መባሉን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ተቋማቱ በ”አገልጋይነት ቀን” ላገለገሉ ሰዎች ምስጋና በመስጠት ያከብራሉ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.