Fana: At a Speed of Life!

ምዕራብ አርሲ ዞን ለመከላከያ ሠራዊት 374 ሰንጋዎችን አበረከተ

አዲስ አበባ፣ ጷጉሜን 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምዕራብ አርሲ ዞን አስተዳዳር የሀገርን ሰላም ለማስጠበቅ እየተዋደቀ ላለው መከላከያ ሠራዊት 28 ሚሊየን ብር የሚገመቱ 374 ሰንጋዎችን አበረከተ።
ድጋፉ በዞኑ አስተዳደር ስር ከሚገኙ 13 ወረዳዎችና ሁለት ከተማ አስተዳደሮች የተሰበሰበ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ድጋፉንም በሀገር መከላከያ ሠራዊት የደቡብ ዕዝ ተረክቧል፡፡
ኢትዮጵያ ከአሸባሪው ህወሓት ጋር እያደረገች ላለው ትግል የዞኑ ሕዝብ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል የምዕራብ አርሲ ዞን አስተዳዳሪ አሕመድ ሀጂ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በተመሳሳይ የሀላባዞን ሕዝብ ለመከላከያ ሠራዊት ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው÷ 30 ሰንጋ፣ 100 የበግ ሙክቶችን፣ 126 ኩንታል በሶ፣ 127 ኩንታል ዱቄት እና 1 ሺህ ደርዘን ውሃ ድጋፍ ማድረጉን የዞኑ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡
እንዲሁም የሲዳማ ክልላዊ ምንግሥት እና ሕዝብ ለመከላከያ ሠራዊት 25 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር የሚገመት÷ 200 ሰንጋዎች፣ 400 ፍየሎች እና በጎችን ጨምሮ የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
ርዕሰ መስተዳደር ደስታ ሊዳሞ በድጋፍ ሽኝቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ አሸባሪው ህወሓት ከኢትዮጵያ እስከሚወገድ የክልሉ ሕዝብ ለመከላከያ ሠራዊት የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲያጠናክር ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በጥላሁን ይልማ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.