Fana: At a Speed of Life!

የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ አዲሱን አመት ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው በተጠናቀቀው አመት እንደ ሀገርና ክልል በርካታ ውጤቶች የተገኙ ቢሆንም ተግዳሮቶችና ፈተናዎች አጋጥመዋል ብለዋል።

በ2014 ዓ.ም የተከናወኑ ውጤታማ ስራዎችን ማጠናከርና የተስተዋሉ ውስንነቶችን መቅረፍ እንዲሁም ያጋጠሙ ፈተናዎችን ለማለፍ ርብርብ ማድረግ ይገባልም ነው ያሉት።

በአዲሱ አመት አሸባሪው ህወሓት በመንግስት የተዘረጋውን የሰላም አማራጭ በመግፋት ለሶስተኛ ጊዜ የከፈተውን ጦርነት በአንድነት መመከት እና የሀገር ሉዓላዊነትና አንድነትን ማስቀጠል አስፈላጊ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ከውስጥም ከውጪም ሆነው ሀገሪቱን ለማተራመስ እና አንድነታችንንና የብልፅግና ጉዟችንን ለማደናቀፍ የሚፈልጉ አካላትን በፅናት መታገል እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የክልሉ ህዝብና መንግስትም በተለይ ሀገርን እየታደጉ ለሚገኙት የሀገር መከላያ ሰራዊትና ለሌሎች የፀጥታ አካላት እያደረጉ የሚገኙት ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

በአዲሱ ዓመት የክልሉን ህዝብ ሁለተናዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ተግባራት እውን ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰራም ነው የገለፁት።

የክልሉን ሰላም ለማጠናከር፣ የህግ የበላይነት እንዲከበርና የክልሉ ህዝብ በሰላም በመቻቻልና በአብሮነት የመኖር እሴት እንዲጎለብት ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው መናገራቸውን ከሐረሪ ክልል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ህዝቡም በሚከናወኑ ተግባራት ተሳትፎውን እንዲያጎለብት ጠይቀዋል።

2015 አዲሱ ዓመትም የሰላም፣ የፍቅር፣ የብልጽግና እንዲሆን ለመላው ኢትዮጵያውያን ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.