የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዙሪክ-ሚላን አዲስ አበባ በረራ ሊጀምር ነው
አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዙሪክ-ሚላን አዲስ አበባ ከጥቅምት 21 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በረራ እንደሚጀምር ተገልጿል።
አየር መንገዱ በሳምንት ሶስት ጊዜ ከስዊዘርላንድ ዙሪክ በመነሳት በጣልያን ሚላን ወደ አዲስ አበባ በረራ እንደሚያደርግ ከዙሪክ አየር መንገድ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በአዲሱ መስመር ተጓዦች ሲሸልስ፣ ደቡብ አፍሪካና ኬንያን ጨምሮ 62 የአፍሪካ መዳረሻዎችን ማግኘት እንደሚችሉ ተጠቁሟል።