Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በ3 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የተገነቡ መኖሪያ ቤቶች አቅም ለሌላቸው ነዋሪዎች ተሰጡ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በ3 ነጥ 2 ሚሊየን ብር ያስገነባቸውን 24 መኖሪያ ቤቶች አቅም ለሌላቸው ነዋሪዎች አስረከበ።

የመኖሪያ ቤቶቹ በክፍለ ከተማው ወረዳ 13 መብራት ሐይል መጠለያ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር የተገነቡ መሆኑ ተገልጿል።

የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ለገሰ የቤቶቹን ቁልፍ በዛሬው ዕለት ለባለእድለኞች አስረክበዋል።

መኖሪያ ቤቱ ከተላለፈላቸው 24 ነዋሪዎች መካከል 6ቱ አካል ጉዳተኞች መሆናቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በክፍለ ከተማው ወጪ በ6 ወራት ውስጥ ግንባታቸው የተጠናቀቀው እነዚህ ቤቶች እያንዳንዳቸው 24 ካሬ ሜትር ስፋት አላቸው ተብሏል።

በክፍለ ከተማው የድሃ ድሃ ተብለው የተለዩ ከ15 ሺህ በላይ ቤት ፈላጊ ነዋሪዎች ይገኛሉ።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.