የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን “ኢንሱሌሽን ብላንኬት” ማምረቻ ፋብሪካ አስመረቀ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ6 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ በሆነ ወጪ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ያስገነባውን የአውሮፕላን “ኢንሱሌሽን ብላንኬት” ማምረቻ ፋብሪካ አስመርቋል።
ፋብሪካው በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ቅጥር ግቢ የተገነባ ነው ተብሏል።
በምርቃት መርሐ ግብሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፣ በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አጎስቲኖ ፓልሴ፣ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።
አቶ ከጣሊያኑ ጀቨን ስካይ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ጋር ስምምነት በማድረግ ለቦይንግ-737 ማክስ አውሮፕላን የሚውል የኢንሱሌሽን ብላንኬት ማምረቻ ፋብሪካን እውን ማድረግ እንደተቻለ ገልጸዋል።
ፋብሪካው የኢትዮጵያን የውጭ ምንዛሬንና የስራ እድል ፈጠራን በማሳደግ ጉልህ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አጎስቲኖ ፓልሴ በበኩላቸው፥ የኢትዮጵያ አየር መንገድና የጣሊያኑ ስካይ ቴክኖ ግሮቭን ግሩፕ ስምምነት ወስደው ፋብሪካውን እውን ማድረጋቸው የጣሊያንና ኢትዮጵያን ትብብር የበለጠ ያሳድገዋል ብለዋል።
በቀጣይም ጣሊያን የኢትዮጵያን እድገትና ብልጽግና በመደገፍ የምታደርገውን በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ትብብር አጠናክራ ትቀጥላለች ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!