በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ መድንን አሸነፈ
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 21 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ መድንን 7ለ1 አሸንፏል፡፡
ፕሪሚየር ሊጉ ትናንት በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም መጀመሩ ይታወሳል፡፡
ዛሬ ከሰዓት በተደረገ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ መድንን 7ለ1 አሸንፏል፡፡
በጨዋታው የቅዱስ ጊዮርጊስን ግቦች እስማኤል ኦሮ አጎሮ፣ቸርነት ጉግሳ፣ቢኒያም በላይ ፣ፍሪምፖንግ ሜንሱ አስቆጥረዋል፡፡
እስማኤል ኦሮ አጎሮ በጨዋታው ሐት ትሪክ ሲሰራ በዚህም የዓመቱ የመጀመርያ ባለ ሐት-ትሪክ መሆን ችሏል፡፡
ኢትዮጵያ መድንን ብቸኛ ግብ ደግሞ ብሩክ ሙሉጌታ አስቆጥሯል፡፡