አቶ ኦርዲን በድሪ በግንባታ ላይ ያለውን የድንገተኛ አደጋዎች መከላከያ ማዕከል ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በሐረር ከተማ እየተገነባ ያለውን የእሳት እና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከያ ማዕከል ጎበኙ፡፡
አቶ ኦርዲን እንደገለጹት÷ ማዕከሉ ለምሥራቅ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ሁሉ አገልግሎት ይሰጣል፡፡
ከማዕከሉ ግንባታ ጐን ለጐን ከወዲሁ አስፈላጊ ግብዓቶችንየማሟላት ሥራ እየተሠራ መሆኑም ተገልጿል፡፡
ለአብነትም ሦስት የእሳት አደጋ መከላከያ ተሸከርካሪዎች ግዢ ለመፈጸም እንቅስቃሴ ተጀምሯል ተብሏል፡፡
ማዕከሉ ከ175 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ በሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ግቢ ውስጥ ነው እየተገነባ የሚገኘው፡፡
ነሐሴ 2014 ግንባታው የተጀመረው ማዕከሉ÷ አሁን ላይ 24 በመቶ መድረሱ እና እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ለማጠናቀቅ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡
የማዕከሉ ግንባታ ሲጠናቀቅ በዋናት ሥድስት የእሳት አደጋ መከላከያ ተሸከርካሪዎችን ማቋም እንደሚችልና ከ5ሺህ ሜትር ኪዩብ በላይ ውኃ መያዝ የሚችል ማጠራቀሚያ እንደሚኖረው ተመላክቷል፡፡
በተሾመ ኃይሉ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!