Fana: At a Speed of Life!

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ለመከላከያ ሰራዊት 49 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 25 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት 49 ሚሊየን ብር የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አደረገ፡፡
 
ድጋፉን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጀዋር ለመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሊዊጅ አስረክበዋል፡፡
 
ከንቲባ ከድር ከተማ አስተዳደሩ ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት በሁለት ዙር የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ እንደነበር አስታውሰው÷የአሁኑ ለ3ኛ ዙር መሆኑን ተናግረዋል።
 
ድጋፉ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሰበሰበ መሆኑን የገለጹት ከንቲባው÷ ለሰራዊቱ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ።
 
ከተደረገው ድጋፍ ውስጥ 30 ሚሊየን የሚሆነው በጥሬ ገንዘብ ሲሆን ÷ 19 ሚሊየን ብሩ ደግሞ የአይነትና የቁሳቁስ ድጋፍ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
 
የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሊዊጅ ጀግናው መከላከያ ሰራዊት ለመላው ኢትዮጵያውያን ሲል ህይወቱን እየሰጠ በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ደጀንነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.