1 ሺህ 447ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል አርብ ይከበራል
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 1 ሺህ 447ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል በሳዑዲ አረቢያ ጨረቃ ባለመታየቷ በአርብ መጋቢት 11 ቀን ይከበራል፡፡
ዛሬ የሸዋል ወር ጨረቃ ባለመታየቷ 1447ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል ከነገ ወዲያ አርብ (ጁምዓ) ተከብሮ እንደሚውል ነው የተገለጸው፡፡
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ተቀዳሚ ም/ፕሬዚዳንት ሼህ አብዱልከሪም ሼህ በድሪን በዓሉን አስመልክቶ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በረመዳን ጾም ወቅት የነበረው የመረዳዳትና መተሳሰብ እሴት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
ሕዝበ ሙስሊሙ የዒድ አልፈጥር በዓልን ሲያከብር የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳትና በመጠየቅ ሊሆን እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡