Fana: At a Speed of Life!

በአራት ክልሎች 16 ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር፣ አማራ፣ ኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች 16 ትምህርት ቤቶችን መገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ፡፡

ስምምነቱን የፈረሙት÷ የ”ሰዎች ለሰዎች” ድርጅት ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሰባስቲያን ብራንዲስ እና የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ  ናቸው፡፡

ለሚገነቡት የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችም÷ 300 ሚሊየን ብር ወጪ እንደሚደረግ በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል፡፡

የሚገነቡት ትምህርት ቤቶች በዓመት በአማካይ 8 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋሉ ተብሏል፡፡

ስምምነቱ በኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች አዳዲስ ትምህርት ቤቶችን መገንባትን ያካተተ ሲሆን÷ በአፋር እና አማራ ክልሎች ደግሞ ከአዳዲስ ግንባታ በተጨማሪ በጦርነት የተጎዱ የትምህርት ቤት ሕንጻዎችን በአዲስ የመተካት ሥራን ያካተተ ነው ተብሏል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ እንደገለጹት÷ የወደሙ ትምህርት ቤቶችን የመገንባቱ ሥራ የሁሉንም ማህበረሰብ ትብብር የሚጠይቅ በመሆኑ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የድርሻውን ሊወጣ ይገባል፡፡

ሰባስቲያን ብራንዲስ በበኩላቸው÷ ሰዎች ለሰዎች ድርጅት የሚገነባቸው ትምህርት ቤቶች አብዛኛዎቹ የግንባታ ግብዓታቸው ከአውሮፓ የሚገቡና ከፍተኛ ጥራት ያላቸው መሆናቸውን ገልጸዋል።

የ16ቱም ትምህርት ቤቶች ግንባታ በዚህ ዓመት እንደሚጀመር እና በሁለት ዓመት ከሦስት ወር ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆኑም ተናግረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.