በክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች የተመራ የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ልዑክ ጅግጅጋ ገባ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች የተመራ የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ልዑክ ጅግጅጋ ገባ፡፡
ልዑኩ ገራድ ዊል ዋል አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ እና በሌሎች የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል ተደርጎለታል፡፡