Fana: At a Speed of Life!

በጎንደር ጓደኛማቾች በ3 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ወጪ ያስገነቡት ት/ ቤት ለአገልግሎት በ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 28 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢንጂነር አክሱማይት አብርሃ እና ጓደኞቿ በጎንደር ከተማ አስተዳደር የተገነቡ 8 ክፍሎች ያሏቸው ባለ 2 ብሎክ የመማሪያ ክፍሎች ግንባታቸው ተጠናቆ ተመርቀዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ባዩህ አቡሃይ ÷ ኢንጂነር አክሱማይት አብርሃ እና ጓደኞቿ በከተማው ያለውን የትምህርት ቤቶች ደረጃ ለማሳደግ እያበረከተ ያለው አስተፅዎ በአርያነት የሚጠቀስ ነው ብለዋል።

በከተማዋ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን ለማሳደግ በግለሰቦች እና በተቋማት እየተደረገ ያለው አስተዋፅኦ የሚያበረታታ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በቀጣይም በከተማዋ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሳደግ አጋር አካላት እያበረከቱት ያለውን አስተዋፅኦ አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።

ኢንጂነር አክሱማይት እና ጓደኞቿ ያስገነቧቸው ት/ቤቶች በከተማዋ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ የትምህርት ተቋማትን ደረጃ በማሳደግ ለመማር ማስተማሩ የሚኖራቸው ጠቀሜታ ከፍ ያለ ነው ብለዋል።

ኢንጂነር አክሱማይት ÷ ከጓደኞቻቸው እና ከአጋር አካላት በተገኘ 3 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው ትምህርት ቤት በመጠናቁ መደሰታቸውን ገልጸዋል።

ግንባታው እንዲጠናቀቅ አስተዋፅዎ ላበረከቱ ግለሰቦች እና አጋር አካላትም ምስጋና ማቅረባቸውን የጎንደር ከተማ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.