Fana: At a Speed of Life!

በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ ቆንጋ ቀበሌ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን የወረዳው ፖሊስ ፅህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የፅህፈት ቤቱ አስተባባሪ ምክትል ኮማንደር ከበደ ብርሃነ እንዳስታወቁት÷አደጋው የተከሰተው ከሞያሌ ወደ ዲላ ሲጓዝ የነበረ ማርቼዲስ መኪና በቆንጋ ቀበሌ መንገድ ጥሶ በመግባቱ ነው፡፡

በተከሰተው አደጋም የመኪናው አሽከርካሪና ባለ ሁለት እግር ሞተር አሽከርካሪ ህይወታቸው ሲያልፍ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት የመኪና ረዳት በዲላ ሪፈራል ሆስፒታል ህክምና እየተደረገለት መሆኑን ከጌዴኦ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.