Fana: At a Speed of Life!

ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ መንገደኞች የ14 ቀናት በልዩ ማቆያ የመቆየት ግዴታ ሰኞ መተግበር ይጀምራል

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ወደ ኢትዮጵያ በሚመጡ ሁሉም መንገደኞች ላይ ተፈፃሚ የሚሆነው የ14 ቀናት በልዩ ማቆያ የመቆየት ግዴታ የፊታችን ሰኞ መተግበር እንደሚጀምር የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ እነዚህ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች በስካይ ላይት እና ጊዮን ሆቴሎች ለ14 ቀናት ተለይተው ይቆያሉ።

ቆይታቸውም በራሳቸው ወጪ የሚሸፈን ይሆናል።

ዲፕሎማቶች ደግሞ በኤምባሲዎቻቸው ተለይተው እንደሚቆዩ የጤና ሚኒስቴር ገልጿል።

የትራንዚት ተጓዦችም እስከ ቀጣዩ ጉዟቸው ድረስ በስካይ ላይት ሆቴል ተለይተው እንደሚቆዩም ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ 30 ሀገራት የሚያደርገውን በረራ በጊዜያዊነት ማቆሙ መገለፁ ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.