Fana: At a Speed of Life!

ባህላዊ እሴቶችን በሙዚቃ መግለፅን ዓላማ ያደረገ የሙዚቃ ኮንሰርት በሚሌኒየም አዳራሽ ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ባህላዊ እሴቶችን በሙዚቃ መግለፅን ዓላማ ያደረገ አንጋፋ አርቲስቶች የሚሳተፉበት የሙዚቃ ኮንሰርት በሚሌኒየም አዳራሽ ሊካሄድ ነው።

የፊታችን ቅዳሜ ጥቅምት 05 ቀን 2015 ዓ.ም የሚካሄደው ‘ማጀቴ’ የተሰኘው ይህ የሙዚቃ ኮንሰርት፥ ሻኩራ ፕሮዳክሽንስ ከሜላ ኢቨንትስ ጋር በመሆን ያዘጋጁት ነው።

በዝግጅቱ ላይ አንጋፋ አርቲስቶች የተለያዩ የሙዚቃ ቅኝቶችን የሚያቀርቡ ሲሆን፥ ተጋባዥ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችም ይገኙበታል፡፡

በመድረኩ ላይም አርቲስት ማህሙድ አህመድ ከረጅም ጊዜ በኋላ የሙዚቃ ስራዎቹን መድረክ ላይ ይጫወታል፡፡

የማጀቴ አልበም ባለቤት የሆነችው ኒና ግርማም ስራዎቿን ለመጀመሪያ ጊዜ ለህዝብ ታቀርባለች፡፡

በተጨማሪም አብነት አጎናፍር፣ ቤቲ ጂ፣ ያሬድ ነጉ፣ ሌንጮ ገመቹ እና ግርማ ተፈራን የመሰሉ ዝነኛ አርቲስቶች የሚሳተፉበት ይህ ኮንሰርት በሚሌኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልፀዋል።

የዝግጅቱ አላማ ባህላዊ እሴቶችን በሙዚቃ አማካኝነት በመግለጽ ታዳሚዎች በሚያደንቋቸው አርቲስቶች ሙዚቃ እንዲዝናኑ ማስቻል መሆኑንም ነው ያስታወቁት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.