Fana: At a Speed of Life!

የእንስሳት መኖ ምርት ከግብር ነፃ ሊደረግ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንስሳት መኖ ምርትን ከግብር ነፃ ለማድረግ የሚያሥችል ስራ እየተሠራ መሆኑን ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በሚኒስቴሩ የመኖ ሃብት ልማት መሪ አሥፈፃሚ አርዓያ አብርሃም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት ከመኖ ምርት ጋር ተያይዞ በተለይም ደግሞ ከዋጋው አንፃር ያለውን ችግር ለማስተካከል አጠቃላይ የመኖ ግብይትን ከቀረጥ ነጻ ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡

ደንብ እየተዘጋጀለት የሚገኘው አሰራሩ ከቀጣዩ ህዳር ወር ጀምሮ ወደ ሥራ ለማሥገባት ዝግጅቱን አጠናቋልም ነው ያሉት ኃላፊው።

ከዚህ በተጨማሪም አርሶ አደሩ እና በእንስሳት ማርባት እና አቅርቦት ስራ ላይ የተሠማሩ አካላት መኖን በአግባቡ እያመረቱ አቅርቦቱን አስተማማኝ ለማድረግ የመኖ ልማት ፕሮጀክት ተቀርፆ ስራ እየተሠራበት እንደሚገኝም ተገልጿል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የእንስሳት መኖ ምርትን ከግብር ነፃ ለማድረግ የወሰነው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የሚገኘው የእንስሳት ተዋፅኦ ምርቶች ዋጋ ለተጠቃሚዎች ከፍተኛ ችግር መፍጠሩን በመገንዘብ ነው ብሏል፡፡

በሰሎሞን ይታየው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.