Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት መንግሥት ቁርጠኛ ነው- አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት መንግሥት ቁርጠኛ መሆኑን የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን ከጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ካቲያ ኮል ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ በኢትዮጵያና በጀርመን መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በውይይ ላይ አቶ ደመቀ ሀገራቱ በኃይል፣ በአየር ንብረት ለውጥ፣ በሰላም እና በጸጥታ ጉዳዮች ላይ በትብብር መሥራት እንዳለባቸው አመላክተዋል፡፡

በሰሜን የሀገሪቱ ክፍል የተፈጠረውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ኢትዮጵያ ቁርጠኛ መሆኗንም አስገንዝበዋል፡፡

ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች በኢትዮጵያ ላይ ያቀረቡት ሪፖርት ፖለቲካዊ ይዘት ያለው እና የተዛባ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ካቲያ ኮል በበኩላቸው÷ በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰተውን ግጭት ለማስቆም የሚደረገውን የሰላም ሂደት ጀርመን ትደግፋለች ማለታቸውን የውጭ ጉይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.