ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከቱርክዬ ፕሬዚዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቱርክዬ ፕሬዚዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ውይይታችን በኢትዮጵያ እና በቱርክዬ መካከል ያለውን ዘላቂ ወዳጅነትና ጠንካራ ትብብር ይበልጥ ያጠናከረ ነው ብለዋል።
በስትራቴጂያዊ የትብብር መስኮች ላይ የሃሳብ ልውውጥ ማድረጋቸውን ጠቁመው የሁለቱን ሀገራት ጥቅም የሚያስከብሩ አጋርነቶችን ለማሳደግ ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት ዳግም አረጋግጠናል ነው ያሉት።
ዘላቂው ግንኙነታችን ሁለቱን ሀገሮች የሚያስተሳስረውን ወዳጅነት ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ሙሉ እምነት አለኝ ብለዋል።