Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ከእንግሊዝ የዌሴክስ ልዕልት ሶፊ ራይስ-ጆንስን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በአፍሪካ ጉብኝት እያደረጉ ካሉት ከእንግሊዝ የዌሴክስ ልዕልት ሶፊ ራይስ-ጆንስን ጋር በተለያዩ ሰብዓዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸው ዓይነ ስውርነትን በማጥፋት ዙሪያ፣ በጦርነት ወቅት የሚደርሱ ጾታዊ ጥቃቶችን በመከላከልና በሠላምና ፀጥታ የሴቶች ሚና ላይ መክረዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ በውይይታቸው ወቅት÷ የልዕልቷ ጥረት የሚያስመሰግን መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ኢትዮጵያም ለእነዚህ የሰብዓዊ ጉዳዮች ትኩረት እንደምትሰጥ መግለጻቸውን ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.