አቶ ደመቀ መኮንን ከዓለምአቀፉ የቀይመስቀል ኮሚቴ ምክትል ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ
አዲ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከዓለምአቀፉ የቀይመስቀል ኮሚቴ ምክትል ፕሬዚዳንት ጂሌስ ካርቦኔር ጋር ተወያዩ፡፡
ውይይቱ የተካሄደው በባሕር ዳር እየተካሄደ ከሚገኘው 10ኛው የጣና ፎረም ጉባዔ ጎን ለጎንነው፡፡
አቶ ደመቀ የዓለምአቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በኢትዮጵያ እያደረጋቸው ላለው የሰብአዊ አገልግሎት ምስጋና አቅርበዋል።
በተለይ በአሁኑ ወቅት በሰሜን ኢትዮጵያ ባለው ግጭት ተጎጂ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ቀይ መስቀል እያደረገ ያለውን ሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት አጠናክሮ እንዲቀጥል መጠየቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡