Fana: At a Speed of Life!

በሴካፋ ከ17 ዓመት በታች የፍጻሜ ጨዋታ ሶማሊያ ሻምፒየን ሆነች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በተካሄደ በሴካፋ ከ17 ዓመት በታች የፍጻሜ ጨዋታ ሶማሊያ ደቡብ ሱዳንን 3 ለ 1 በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሆናለች፡፡
ከፍጻሜው ቀደም ብሎ በተካሄደ የደረጃ ጨዋታ ታንዛኒያ ዩጋንዳን በመለያ ምት 4ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፏ ይታወቃል፡፡
የምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ማኅበራት ምክር ቤት (ሴካፋ) በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ከመስከረም 23 እስከ ጥቅምት 5 ቀን 2015 በአበበ በቂላ ስታዲየም ተካሂዷል፡፡
በውድድሩ አንደኛ እና ሁለተኛ የወጡት ሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን በመጋቢት ወር 2015 ዓ.ም በአልጄሪያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ከ17 ዓመት በታች የእግር ኳስ ውድድር ዞኑን ወክለው ይሳተፋሉ፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.