አሰልጣኝ ስዩም ከበደ የሲዳማ ቡና አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አሰልጣኝ ስዩም ከበደ የሲዳማ ቡና ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሾመዋል፡፡
በ2013 የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማን ለሻምፒዮናነት ያበቁት አሰልጣኝ ስዩም ከበደ በዘንድሮው የውድድር አመት አስከፊ የሚባል አጀማመር ላይ የሚገኘውን ሲዳማ ቡናን በዋና አሰልጣኝነት ተረክበዋል፡፡
በዘንድሮ የዝውውር መስኮት ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረግ አዳዲስ ተጫዋችን ማስፈረም የቻለው ሲዳማ ቡና የሚጠበቀውን ውጤት ማግኘት አልቻለም፡፡
እስካሁን ባደረጋቸው ሦስት ጨዋታዎች ከድሬዳዋ ከተማ 2 ለ 2 ሲለያይ በሀድያ ሆሳዕና 4 ለ1 እንዲሁም በፈረሰኞቹ ደግሞ የ5 ለ 1 ሽንፈትን አስተናግዷል፡፡
ክለቡ በሶስት ጨዋታዎች ማግኘት ከነበረበት 9 ነጥብ ውስጥ 1 ነጥብ ብቻ በማስመዝግብ የሊጉ ግርጌ ላይ ይገኛል፡፡