ካሪም ቤንዜማ የ2022 ባሎን ዶር አሸናፊ ሆነ
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 8 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን እና የሪያል ማድሪዱ የፊት መስመር ተጫዋች ካሪም ቤንዜማ የ2022 ባሎን ዶር ሽልማትን አሸነፈ።
ፍራንስ ፉትቦል ለ66ኛ ጊዜ ባካሄደው ምርጫ ካሪም ቤንዜማ ሽልማቱን ለመጀመሪያ ጊዜ አሸንፏል።
ቤንዜማ ባለፈው የውድድር አመት ከስፔኑ ሃያል ሪያል ማድሪድ ጋር ስኬታማ ጊዜን አሳልፏል።
ከክለቡ ጋር የስፔን ላ ሊጋን እንዲሁም የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን አሳክቷል።
ከዚህ ባለፈም በግሉ 44 ግቦችን በማስቆጠር ስኬታማ ነበር።
ቤንዜማ ሽልማቱን ከተቀበለ በኋላ ለስኬቱ ቤተሰቦቹን እና የቡድን አጋሮቹን አመስግኗል።
ሴኔጋላዊው አጥቂ ሳዲዮ ማኔ 2ኛ ደረጃን ሲይዝ ቤልጂየማዊው አማካይ ኬቨን ደ ብሩይነ እና ፖላንዳዊው አጥቂ ሮበርት ሎዋንዶውስኪ ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘው አጠናቀዋል።
የእንግሊዙ ሻምፒዮን ማንቼስተር ሲቲ ደግሞ የዓመቱ ምርጥ ክለብ ሽልማትን አሸንፏል።