Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ አካላት የእውቅና አሰጣጥ መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል በ2014 በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ፈጻሚዎች እና ተቋማት የእውቅና አሰጣጥ መርሐ ግብር በወላይታ ሶዶ ከተማ ተካሄደ ።

በመርሐ ግብሩ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ፣ የደቡብ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋጤ ስርሞሎ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

በመድረኩ ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ በ2014 በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ፈጻሚዎች እና ተቋማት እውቅና የሚሰጡ መሆኑን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በመንግስታት ለውጥ ውስጥ የማይናወጥ ሚና ኖሮት ሀገርን የሚያስቀጥል ህዝብን የሚያገለግል፣ የአንድ ሀገር ዘላቂነት እና አስተማማኝነት የሚወሰንበት ተቋም ነው ብለዋል።

የሪፎርም ስራዎች የተቋምን ዘላቂነት የሚያጸኑ ስራዎች፣ የህዝብ አገልጋይነትን ታሳቢ ያደረጉ ተግባራት፣ ሁልጊዜም ቢሆን ለሀገር ግንባታ ለህዝብ አገልግሎት ተደራሽነት አስፈላጊ መሆናቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።

ባለፉት ዓመታት ሀገር በብዙ ፈተናዎች ውስጥ ሆና በክልሉ አበረታች ስራዎች ማከናወን መቻሉንም ነው ያስረዱት።

አገልጋዩም በአንድ በኩል ሀገርን ከጠላት እየተከላከለ እና የደጀንነት ሚናውን እየተወጣ በሌላ በኩል ደግሞ የተጣለበትን የህዝብ አደራ በብቃት መፈጸም መቻሉን ጠቅሰዋል።

በክልሉ በግብርና፣ በትምህርት፣ በጤና፣ ህዝብን በማገልገል ረገድ የተገኙ ለውጦች እና በሌሎችም መስኮች ለታየው አፈጻጸም አገልግሎት ሰጪ ተቋሙ የትጋት ውጤቶች ናቸው ብለዋል።

እውቅና የተሰጣቸው ተሸላሚዎች አርዓያ ሆነው በርካታ ተከታዮችን ማፍራት እንዳለባቸውም ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.