Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት ተቀባይነት የለውም ሲል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሉዓላዊት ሀገር የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት ኢፍትሐዊ አካሄድ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም ሲል የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገለጸ።

ምክር ቤቱ “ለኢትዮጵያ እቆማለሁ፤ ድምጼን አሰማለሁ” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደውን ሰልፍ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ÷ አንዳንድ የውጭ ኃይሎች በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር የያዙትን አቋም በጽኑ አውግዟል።

የተባበሩት መንግሥታትና የአውሮፓ ሕብረት በኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ ለመጣል የያዙት አቋም የሀገሪቱን ንጹሃን የሚጎዳ ከመሆኑም በላይ በሉዓላዊት ሀገር የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት በመሆኑ ተቀባይነት የለውም ሲል ምክር ቤቱ አውግዟል፡፡

እነዚህ የውጭ ኃሎች ከዚህ አቋማቸው ታርመው ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት ለማሳካት ከኢትዮጵያሕዝብ ጎን እንዲቆሙ ሲል ምክር ቤቱ ጠይቋል፡፡

በአፍሪካ ሕብረት የተጀመረውን የሰላም ውይይት ከግቡ ለማድረስ የበኩላቸውን እንዲወጡም ነው ም/ቤቱ የጠየቀው፡፡

ነገ እና ከነገ በስቲያ በአዲስ አበባ እና በተለያዩ ክልልሎች “ለኢትዮጵያ እቆማለሁ፤ ድምጼን አሰማለሁ” በሚል መሪ ሐሳብ በሚካሄደው ሰልፍ ኢትዮጵያውያን እንዲሳተፉ ምክር ቤቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.