የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት በአጋሮ ከተማ ያስገነባው የዳቦ እና ዱቄት ፋብሪካ ተመረቀ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት በአጋሮ ከተማ ያስገነባው የዳቦ እና ዱቄት ፋብሪካ ተመረቀ፡፡
ፋብሪካው በቀን 300 ሺህ ዳቦና 42 ቶን ዱቄት የማምረት አቅም አለው።
ፋብሪካውን ገንብቶ ለማጠናቀቅ ሰባት ወራት የፈጀ ሲሆን÷ የግንባታ ሥራውም በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እና ሂቤይ ፒንግል ማሽነሪስ አጋርነት ነው የተከናወነው፡፡
የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት በ11 ከተሞች ተመሳሳይ አቅም ያላቸው ዳቦና ዱቄት ፋብሪካዎችን በጋራ ለመገንባት ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ጋር ከተፈራረመ በኋላ በአጋሮ የተመረቀው የመጀመሪያው ነው፡፡
የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ከተማ በቀን 1 ሚሊየን ዳቦ የሚያመርት ፋብሪካ አስገንብቶ ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡
በአልዓዛር ታደለ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!