Fana: At a Speed of Life!

የአመራሩን የተግባር አንድነት ለማጠናከር ሰፊ ጥረት ማድረጉን የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአመራሩን የተግባር አንድነት ለማጠናከር ሰፊ ጥረት መደረጉን የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ ተናገሩ፡፡

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና የፓርቲ የ2015 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት አፈፈፃፀም ግምገማ በአዳማ ገልማ አባገዳ እየተካሄደ ነው።

የጽህፈት ቤት ኃላፊው አቶ ፍቃዱ ተሰማ በአንዳንድ አመራሮች መካከል ወጥ የሆነ የአመለካከት ውስንነት መኖሩ ክልሉን ዋጋ እንዳስከፈለው ገልፀው፥ ይህንንም ለማስተካከል ሰፊ ጥረት ተደርጓል ብለዋል።

በክልሉ አንዳድን አካባቢዎች የገጠሙ የሰላም ዕጦት ችግሮችን በመቅረፍ አካባቢዎቹን ወደ ነበሩበት ሰላም ለመመለስ የክልሉ የፀጥታ ኃይል ከፌደራል የፀጥታ መዋቅር ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን አንስተዋል።

የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ስራዎች በክልሉ መከናወናቸውን ያነሱት ኃላፊው፥ ካለው ፍላጎት አንፃር በቂ ባለመሆኑ ትኩረት ተሰጥቶት መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል።

በግምገማ መርሀ ግብሩ የተለያዩ የክልል የስራ ኃላፊዎች እና የዞን አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በወንድሙ አዱኛ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.