ከንቲባ አዳነች አቤቤ ወጣቶች በበጎ ፈቃድ ሥራዎች ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረቡ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የከተማዋ ወጣቶች በተለያዩ ማኅበራዊና የበጎ ፈቃድ ሥራዎች ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረቡ፡፡
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ በድህረ ምርጫ የከተማዋን ነዋሪዎች ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡ የ90 ቀናት ዕቅዶች ላይ በመወያየት ወደ ተግባር ገብተናል ብለዋል።
ለዚህ ዕቅድ የላቀ ስኬታማነት መላው የከተማችን ነዋሪዎች፣ ባለሀብቶችና ወጣቶች እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ በተለያዩ ማኅበራዊና የበጎ ፈቃድ ሥራዎች ላይ በንቃት በመሳተፍ ማኅበራዊ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ ጥሪ አስተላልፋለሁ ነው ያሉት።