Fana: At a Speed of Life!

ለሸኔ በሎጅስቲክ አቅራቢነት በመስራት የተጠረጠረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሸኔ በሎጅስቲክ አቅራቢነት በመስራት የተጠረጠረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የደቡብ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ተጠርጣሪው በደቡብ ክልል ጋሞ ዞን አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ሻራ ተብሎ ከሚጠራዉ አካባቢ በተደበቀበት በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉ ነው የተገለፀው፡፡

የአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ክበበው አዳል እንደተናገሩት ዳርጌ ጎበና የተባለው ይህ ተጠርጣሪ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን አባያ ወረዳ ለሽብር ቡድኑ ኦነግ ሸኔ ሎጅስቲክ ሲያቀርብ እንደነበር ገልፀዋል፡፡

ተጠርጣሪው በኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል ፖሊስ በጥብቅ ሲፈለግ የቆየ ሲሆን ከጉጂ ዞን አባያ ወረዳ በተገኘ መረጃ  በተደረገ ክትትል ሻራ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ በግለሰብ ቤት ተደብቆ  በቁጥጥር ስር መዋሉን ተናግረዋል፡፡

በፍርድ ቤት የማደኛ ትእዛዝ የተያዘው ተጠርጣሪ ለኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ተላልፎ መሰጠቱንም ነው አዛዡ የተናገሩት፡፡

በተለይም የሽብር ቡድኑ በሚንቀሳቀስባቸው አካባቢዎች  ህብረተሰቡ ፀጉረ ልውጥ ሰው በሚመለከትበት ወቅት በአቅራቢያው ለሚገኝ ፖሊስ እንዲሳውቅ አዣዡ ጥሪ ማቅረባቸውን ከደቡብ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.