ኮረም ወደ ሠላማዊ እንቅስቃሴ እየተመለሰች ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮረም ከተማ ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እየተመለሰች እንደምትገኝ ነዋሪዎቿ ተናገሩ።
ባለፉት ዓመታት አሸባሪው ህወሓት ጦርነት በመክፈቱ ምክንያት የከተማዋ ነዋሪዎች በኑሮ ውድነት ሲሰቃዩ እንደቆዩ እና በሠላም ወጥቶ መግባት የማይችሉበት ደረጃ ላይ ደርሰው እንደነበር ተናግረዋል።
አሁን ላይ ኮረምና አካባቢው ላይ ሠላም በመስፈኑ በሠላም ወጥተው እየገቡ መኾናቸውን የአሚኮ ዘገባ አመላክቷል፡፡
ባለፉት ወራት ግብይት ተቋርጦ እንደነበር የገለጹት ነዋሪዎቹ አሁን ላይ ሠላማዊ በኾነ መንገድ ገበያ መጀመሩንም ነው የተናገሩት።
ለወገን ጦር ደጀን በመኾን ከአካባቢው የመንግሥት የፀጥታ መዋቅር ጋር ተቀናጅተው ለሰላም ዘብ እንደሚቆሙም ነዋሪዎቹ አረጋግጠዋል።