Fana: At a Speed of Life!

ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት እድሳት ተጠናቆ ተመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 19 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት እድሳት ተጠናቆ ተመረቀ።

ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት እድሳቱን ጨርሶ ለአገልግሎት ክፍት ተደርጓል።

በ1927 ዓ.ም እንደተመሰረተ የሚነገርለትና በርካታ አንጋፋ ከያንያንን ያፈራው ሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት በ1994 ዓ.ም አሁናዊ ገፅታውን ይዞ እንዲሰራ መደረጉ ይታወሳል።

የነበረውን ገፅታ በጠበቀ መልኩ 2013 ዓ.ም የጀመረው የእድሳት ስራ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.