Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ተቋማት ለሀገር ዕድገትና ለዓለም አቀፍ ውድድር ብቁ ለመሆን ለጥራት ልዩ ትኩረት ሊሰጡ ይገባል-ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ተቋማት ለሀገር ዕድገትና ለዓለም አቀፍ ውድድር ብቁ ለመሆን ለምርትና አገልግሎት ጥራት ልዩ ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ገለጹ።

9ኛው ሀገር አቀፍ የተቋማት የጥራት ሽልማት መርሐ ግብር ዛሬ በታላቁ ቤተ-መንግስት ተካሂዷል፡፡

በተለያዩ ዓለም ዓቀፍ መስፈርቶች ብቁ የሆኑ ከ40 በላይ የምርትና አገልገሎት ሰጪ ድርጅቶችም የጥራት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ በዚህ ወቅት÷ እንደ ሀገር ለማደግ፣ የህዝባችንን ኑሮ ለመለወጥና በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን ጥራት ማዕከላዊ የትኩረት አቅጣጫ መሆን አለበት ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በኢትዮጵያ በጥራት ዙሪያ የታዩ ለውጦች ቢኖሩም ብዙ መስራት እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል።

ጥራት ገደብ የለውም ያሉት ፕሬዚዳንቷ÷ ከሌሎች ሀገራት በጎ ተሞክሮዎችን በመውሰድ ለሀገራችን ማምጣትም የተቋሞቻችን ባህል ሊሆን እንደሚገባ አንስተዋል።

እንደ ሀገር ተወዳዳሪ ኢኮኖሚ ለመገንባት የጥራት ስራ የምርጫ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ መሆኑን ሁሉም ሊገነዘብ እንደሚገባ ተናግረዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.