አዲስ አበባ የአፍሪካውያን ወንድማማችነትና ህብረት መገለጫ ሆና እየቀጠለች ነው-ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ ዛሬም የአፍሪካዊያን ወንድማማችነትና ህብረት መገለጫ ሆና እየቀጠለች ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ፡፡
ከንቲባዋ ዛሬ የተከፈተውን የመጀመሪያውን የአፍሪካ ወጣቶች ጉባኤ ምክንያት በማድረግ የከተማ አስተዳደሩ ባዘጋጀው የእራት ፕሮግራም ተገኝተው ÷ አዲስ አበባ የመላው አፍሪካዊያን መዲና ናት ብለዋል፡፡
አዲስ አበባ የፓንአፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ ማዕከል ሆና ዘመናትን ተሻግራለች ያሉት ከንቲባ አዳነች ዛሬም የአፍሪካዊያን ወንድማማችነትና ህብረት መገለጫ ሆና እየቀጠለች ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡
የመጀመርያውን የአፍሪካ ወጣቶች ጉባኤ ለመሳተፍ ወደ ከተማዋ ለመጡት ወጣቶችና እንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል በማድረጋችን ደስ ብሎናል ሲሉም አስፍረዋል፡፡
ለእንግዶችም መልካም ቆይታ እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል፡፡