Fana: At a Speed of Life!

መንግስት ነፃ በወጡ የትግራይ ክልል አካባቢዎች ሰብዓዊ ድጋፍ ማቅረብ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት ነፃ በወጡ የትግራይ ክልል አካባቢዎች ሰብዓዊ ድጋፍና የህክምና መድሃኒት ማቅረብ ጀመረ፡፡

የፊደራል አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም እንደገለፁት፥  መንግስት ከአሁን ቀደም ያደርግ የነበረውን ያልተቋረጠ ሰብዓዊ ድጋፍ ለትግራይ ክልል እያቀረበ መሆኑን ገልፀዋል።

መንግስት በገባው ቃል መሰረት ነፃ በወጡ የትግራይ ክልል አካባቢዎች ከ3 ሺህ ኩንታል በላይ የጥራጥሬና አልሚ ምግቦች በመጀመሪያው ዙር ማጓጓዣ መጀመሩን አብራርተዋል።

መንግስት ያልተቋረጠ ሰብዓዊ ድጋፍን ለትግራይ ክልል እያቀረበ ነው ያሉት አምባሳደሩ፥ በተጨማሪም 3 የጭነት ተሸከርካሪዎች የህክምና መድሃኒትና መገልገያ ቁሳቁሶች ጭነው ነፃ በወጡ የክልሉ አካባቢዎች እየተላኩ ነው ብለዋል።

በጦርነቱ ተቋርጠው የቆዩ መደበኛ አገልግሎቶች እንዲጀምሩና የወደሙ ተቋማት መልስው አገልግሎት እንዲሰጡ የመልሶ ጥገና  ስራዎችን  መንግስት በሰፊው እየሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በቀጣይም መንግስት በትግራይ ክልል የሚያደርገውን ሰብዓዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ኮሚሽነሩ አስረድተዋል፡፡

 

በምናለ አየነው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.