Fana: At a Speed of Life!

የኢፌዲሪ መንግሥት በሴዑል በዜጎች ላይ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መንግሥት በደቡብ ኮሪያ ሴዑል ዓመታዊ በዓል በማክበር ላይ በነበሩ ዜጎች በደረሰው ድንገተኛ አደጋ የሰው ህይወት በመጥፋቱ የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገለጸ፡፡

በየዓመቱ በሚከበረው “ሃሎዊን” በዓል በደረሰው የመገፋፋት አደጋ በርካቶች ለሞት እና ለአካል ጉዳት ተዳርገዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት በዚህ አሰቃቂ አደጋ ሕወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች እና ወዳጅ ዘመዶች መጽናናትን ተመኝቷል፡፡

የኢፌዲሪ መንግሥት በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከደቡብ ኮሪያ ሪፐብሊክ መንግሥትና ሕዝብ ጎን መሆኑን አረጋግጧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.