Fana: At a Speed of Life!

አርሜኒያ እና አዘርባጃን በናጎርኖ ካራብክ አካባቢ ወታደራዊ ሀይል ላለመጠቀም ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አርሜኒያ እና አዘርባጃን የድንበር ግጭታቸውን ለመፍታት በናጎርኖ ካራብክ ተራሮች አካባቢ ላይ ወታደራዊ ሀይል ላለመጠቀም ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታወቁ።

የአዘርባጃኑ ፕሬዚዳንት ኢሃም አሊዬቭ እና የአርሜኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኒኮል ፓሺንያን የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በተገኙበት ተወያይተዋል።

በዚህ ወቅትም በሁለቱ ሀገራት ድንበር አካባቢ የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት ወታደራዊ አማራጭን ላለመጠቀም መስማታቸውን አስታውቀዋል።

መሪዎቹ በጋራ ባወጡት መግለጫም በተፈጠሩ አለመግባባቶች ዙሪያ ውይይት ለማድረግ እና ሉዓላዊነታቸውን እና የግዛት አንድነታቸውን ባስከበረ መልኩ ልዩነቶቻቸውን ለመፍታት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ነው የገለጹት።

ስምምነቱ የተደረሰው በሁለቱ የቀድሞው ሶቭየት ህብረት ሀገራት አዋሳኝ አካባቢ በሆነው የናጎርኖ ካራባክ ተራራም አካባቢ ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ ነው፡፡

አካባቢው የአዘርባጃን ግዛት እንደሆነ ቢታሰብም በስፍራው በርካታ አርሜኒያውያን እንደሚኖሩበት ይነገራል።

ባለፈው ወር በሁለቱ ሀገራት መካከል በተፈጠረው አለመግባባት  ወደ 286 የሚጠጉ ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን ፕረስ ቲቪ በዘገባው አስታውሷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.