Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት በሰሜን ዕዝ ላይ የፈፀመው ጥቃት መታሰቢያ ነገ በተለያዩ ክልሎች ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሽብርተኛው ህወሓት በመከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ የፈፀመው ጥቃት ሁለተኛ ዓመት መታሰቢያ ነገ በሲዳማና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በተለያዩ ዝግጅቶች ይካሄዳል፡፡

የሲዳማ ክልል ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ ኢያሱ ዳዊት እንደገለፁት÷ መታሰቢያው በክልሉ በሁሉም ወረዳዎች የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ክብር በሚያጎሉ ዝግጅቶች ይከናወናል፡፡

በሠራዊቱ ተጋድሎ እና በሕዝቡ የደጀንነት ሚና ላይ ያተኮረ ውይይት እንደሚካሄድ የክልሉ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

በተመሳሳይ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሁሉም ወረዳዎች፣ ከተማ አስተዳደሮች የሚገኙ ነዋሪዎች፣ የመንግስት ሠራተኞች፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት አስበው እንደሚውሉ የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.