Fana: At a Speed of Life!

ህብረቱ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ሀገራት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከላከያዎች በማሰራጨቱ እየተወጣች ላለችው ሚና ምስጋና አቀረበ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  የአፍሪካ ህብረት ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ – ጃክ ማ ኢንሽዬቲቭ አማካኝነት ለአፍሪካ ሀገራት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከላከያዎች በማሰራጨቱ እየተወጣች ላለችው ሚና ምስጋና አቀረበ።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊመቀመንበር ሙሳ ፋኪ መኸመት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በላኩት ደብዳቤ፥ ቁሳቁሶቹን በመረከብ እና ለሁሉም አባል ሀገራት በፍጥነት ለማድረስ ለሰጡት አመራር ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ቁሳቁሶቹ በፍጥነት እንዲሰራጩ የህብረቱ አካል ለሆነው የአፍሪካ በሽታ መከላከል ማዕከል /ሲ ዲ ሲ/  ለሰጡት አመራር እና ምክርም ሊቀመንበሩ አመስግነዋል።

እነዚህ ቁሳቁሶች በፍጥነት እንዲደርሱም ሁሉም አባል ሀገራት የዓየር ክልላቸውን እንዲከፍቱ እና አስፈላጊውን ሁኔታዎች እንዲያሟሉ ማስታወሻ ለሀገራቱ እንደሚልኩም ገልፀዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና ቻይናዊው ባለሃብት ጃክ ማ በጋራ በወሰዱት ኢኒሼቲቭ አማካኝነት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን በአፍሪካ ለመከላከል የሚያግዙ የሕክምና መርጃ ቁሳቁሶች ወደ ተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በመድረስ ላይ ናቸው።

ለእያንዳንዱ የአፍሪካ ሃገርም ቫይረሱን ለመለየት የሚረዱ 20 ሺህ መመርመሪያዎች፣ 100 ሺህ የፊት ጭምብል እና የህክምና ባለሙያዎች የሚለብሷቸው 1 ሺህ መከላከያ ልብሶች በመሰራጨት ላይ ይገኛሉ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.