Fana: At a Speed of Life!

ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ከባለድርሻ አካላትጋር እየመከረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ በተሣታፊዎች መለያ ረቂቅ እና አጀንዳ በማሠባሰብ አሠራር እና ሥርዓት ላይ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በደሴ ከተማ ውይይት እያደረገ ነው፡፡

በቆይታው ስለ ሀገራዊ ምክክሩ ፅንሰ-ሐሣብ ፣ስለ ኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅና ምክክርን በተመለከተ፣ ኮሚሽኑ ስለሚያካሂዳቸው ተግባራት ውይይት ይደረጋል ተብሏል፡፡

የምክክር ተሣታፊዎች መለያ ረቂቅ ላይ እና አጀንዳ የማሰባሰብ ሥርዓት ምንነት ላይ የጋራ አቋም ይያዛል ተብሎም ይጠበቃል፡፡

ምክክር ችግሮችን መጋፈጥ የሚጠይቅ፤ የጋራ ተሣትፎንና ባለቤትነትን የሚጠይቅ ነው ሲሉ ኮሚሽነር ዶክተር አምባዬ ኦጋቶ ተናግረዋል፡፡

በሀገራዊ ምክክር ወቅት ፍረጃን ማቆም፣ ግምታዊ መላ ምቶችን ማስወገድ፣ በጥልቀት ማዳመጥ ፣ መጠየቅ እና ራስን መመርመር ያስፈልጋልም ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የተለያዩ የፓለቲካ የማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ የታሪክ አረዳድ እይታዎች አሉ ያሉት ኮሚሽነሩ ሀገራዊ ምክክር ማለት ደግሞ እነዚህ ልዩነቶች ከሀገር አንድነትና ተጠቃሚነት አንጻር ያላቸውን እይታ መረዳትና ራዕያቸው ትልቋን ሀገር እንዲያደርጉ ማድረግ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ይህ ምክክር ደግሞ ያሉ ግጭቶችን መፍታት ያስችላል፤ ልማትንም ማፋጠን ያስችላል ብለዋል፡፡

በመርሐ-ግብሩ የደቡብ ወሎ ዞን አመራር አካላት ፣ የደሴና ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር አመራር አካላት እንዲሁም የደቡብ ወሎ ዞን ወረዳዎች አመራር አካላት ተገኝተዋል፡፡

በተመሳሳይ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በጎንደር ከተማ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር እየመከረ ነው።

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ወይዘሮ ሂሩት ገብረስላሴ÷ኮሚሽኑ በቅድመ ዝግጅት ሂደት በክልሎች ተከታታይ ውይይቶችን በማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር መምከሩን ገልጸዋል።

ዛሬ ደግሞ በጎንደር ከተማ ከዞንና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች፣ ከንቲባዎችና ልዩ ልዩ የሲቪክ ማህበራት ጋር እየመከረ ይገኛል ያሉ ሲሆን÷ ለሁለት ቀናትም እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡

በአለባቸው አባተና ምናለ አየነው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.