Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሥራ እና ክኅሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ፕሬዚዳንትና ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ሪታ ፎይ ከሚመራ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱም ፋውንዴሽኑ 30 ሚሊየን ለሚሆኑ የአፍሪካ ወጣቶች ፣ ምቹና አስተማማኝ የሥራ ዕድል ለመፍጠር 75 በመቶ የሚሆነውን በጀት አፍሪካ ውስጥ ለሚተገብራቸው የልማት ስራዎች መመደቡ ተገልጿል፡፡
 
ኢትዮጵያ የያዘችው ፈጣን የለውጥ ሂደትም በፋውንዴሽኑ ቀዳሚ ተመራጭ እንዳደረጋት ወይዘሮ ሙፈሪሃት በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ የተለያዩ ቦታዎች በመገኘት የሥራ ዕድል ፈጠራ ተግባራት ያሉበትንደረጃ መመልከቱንም ጠቁመዋል፡፡
 
ከትምህርት፣ቱሪዝምና ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴሮች ጋር በመሆንም እንደ ሀገር የቅድሚያ ቅድሚያ በተሰጣቸው ዘርፎች እና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ገለጻ መደረጉ ተመላክቷል፡፡
 
የፋውንዴሽኑ አመራሮች በለውጥ ሂደቱ የተከናወኑ ተግባራትን አድንቀው÷ በተመረጡት የኢትዮጵያ የልማት ዕቅዶች ላይ የቅርብ የልማት አጋር እንደሚሆኑ አረጋግጠዋል፡፡
 
ወ/ሮ ሙፈሪሃት÷ሪታ ፎይ እና ልዑካቸው የልማት ውጥኖቻችንን ለመደገፍ ላሳዩት ቁርጠኝነትና በትብብር ማዕቀፉ ላላቸው ከፍተኛ አስተዋፅዖ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.