Fana: At a Speed of Life!

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የ2 ወራት የግንባር ቆይታቸውን አጠናቀው ወደ ጠቅላይ መምሪያ ቢሯቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)  የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ መንግሥት ከህወሓት ጋር ያደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የሁለት ወራት የግንባር ቆይታቸውን አጠናቀው ወደ ጠቅላይ መምሪያ ቢሯቸው ተመልሰዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከውጊያ ኮማንድ ፖስት ወደ መደበኛ ማዘዣ ቢሯቸው ከተመለሱ በኋላም በመንግሥት እና በህወሓት በተደረገው ስምምነት መሠረት በጥቂት ቀናት ወስጥ ከህወሓት ወታደራዊ አመራሮች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ የሚጠበቅ መሆኑን የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ያመለክታል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.