የሲዳማ ክልል ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የአይነትና የገንዘብ ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የሲዳማ ክልል ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ከ39 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የአይነትና የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ደስታ ሌዳሞ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት ÷ ቀደም ሲል የክልሉ መንግስት ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡
አሁን ላይም የክልሉ መንግስት ከ29 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የአይነት ድጋፍ እንዲሁም በጥሬ ገንዘብ 10 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ ድጋፉ ከመላው የክልሉ ህዝብ የተሰበሰበ መሆኑን ገልፀው፤ ምስጋና ማቅረባቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡