Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የቱሪዝም ንግድ ትርኢት ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በየዓመቱ ለንደን ከተማ በሚደረገው እና በዓለማችን ቀዳሚ ከሆኑት የቱሪዝም ንግድ ትርዒቶች አንዱ በሆነው ወርልድ ትራቭል ማርኬት 2022 ላይ እየተሳተፈች ነው፡፡

ከድህረ ኮሮና በኋላ በተደረገው የዘንድሮው አውደርዕይ ላይ ከ3 ሺህ 437 በላይ የአገልግሎትና ምርት አቅራቢዎች እየተሳተፉ ነው፡፡

በቱሪዝም አውደ ርዕዩ ዘጠኝ የኢትዮጵያ አስጎብኚ ድርጅቶች እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዲሁም በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በጋራ እየተሳተፉ መሆኑን የቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

የወርልድ ትራቭል ማርኬት የቱሪዝም አውደ ርዕይ ለኢትዮጵያ የጎብኚ አመንጭ ከሆኑት ሀገራት መካከል አንዷ በሆነችው እንግሊዝ የሚደረግ ሲሆን÷ ለኢትዮጵያ ጎብኚ አመንጭ የሆኑ ሌሎች የአውሮፓ ሀገራትን ለማግኘትም ያግዛል ነው የተባለው፡፡

በቱሪዝም አውደ ርዕዩ ላይ የሀገራት የቱሪዝም ሚኒስትሮች በቱሪዝም አጠቃላይ እድገት ላይ እንደሚወያዩ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ የጉዞ ፀጸሐፊዎች እና አስጎብኚ ድርጅቶችን ያካተተ ውይይት እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.