Fana: At a Speed of Life!

የአርቲስት ዓሊ ቢራ አስከሬን የሽኝት ሥነ ስርዓት በወዳጅነት ዐደባባይ ተካሔደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአርቲስት ዓሊ ቢራ አስከሬን የሽኝት ሥነ ስርዓት በአዲስ አበባ ከተማ የወዳጅነት ዐደባባይ ተካሔደ፡፡

በወዳጅነት ዐደባባይ በተካሔደው የአስከሬን ሽኝት ሥነ ስርዓት ላይ÷ የአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች፣ የሙያ አጋሮች፣ የሐይማኖት አባቶች እንዲሁም ታዋቂ ግለሰቦች እና አድናቂዎቹ ተገኝተዋል፡፡

የአርቲስት ዓሊ ቢራ አስከሬን በቢሾፍቱ ከተማ ከሚገኘው የአርቲስቱ መኖሪያ ቤት ዛሬ ማለዳ ወደ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መሸኘቱ ይታወቃል፡፡

እንዲሁም ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች እና የአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ ወዳጆች እና አድናቂዎች በተገኙበት ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ወዳጅነት ዐደባባይ በክብር ተሸኝቷል፡፡

በዚሁ መሠረት አሁን ላይ በወዳጅነት ዐደባባይ የሽኝት ሥነ ስርዓቱ ተካሂዷል፡፡

የአርቲስት ዓሊ አስከሬን በወዳጅነት ዐደባባይ የክብር እና የጀግና ስንብት ከተደረገለት በኋላም ወደ ትውልድ ስፍራው ድሬዳዋ ተሸኝቷል፡፡

በድሬዳዋ ስታዲየም የሽኝት መርሐ ግብር ከተካሄደ በኋላም የቀብር ሥነ ስርዓቱ በለገሀሬ የሙስሊም መካነ መቃብር ይፈጸማል፡፡

አርቲስት ዓሊ በአዳማ አጠቃላይ ሆስፒታል በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ጥቅምት 27 ቀን 2015 ዓ.ም በ75 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ይታወሳል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.