የአማራ እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች የወባ በሽታ ሥርጭት ለመቀነስ እየሠሩ መሆኑን ገለጹ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የአማራ እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች በከፍተኛ ደረጃ የወባ በሽታ ስርጭትን ለመቀነስ የሚያስችል ሥራ መጀመራቸውን ተናግረዋል።
የአማራ ክልል የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ በላይ በዛብህ ለፋናብርድካስተንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት ÷ የወባ በሽታ በስፋት በተከሰተባቸው አካባቢዎች የቤት ለቤት ሕክምናዎች መስጠት ተጀምሯል።
አጎበር እና የመሳሰሉትን ግብዓቶች ለማዳረስም እየተሰራ እንደሆነ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል 46 ወረዳዎች ላይ የወባ በሽታ መከሰቱም ተጠቁሟል፡፡
የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ኃይሌ ዘውዴ ÷ የበሽታው ሥርጭት እየጨመረ በመሆኑ በሁሉም ወረዳዎች የመከላከል ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
የግብዓት እጥረቶች መኖራቸውን ተከትሎም ከጤና ሚኒስቴር ጋር እየሠራን ነው ብለዋል፡፡
በዙፋን ካሳሁን