መከላከያ ሰራዊት በትግራይ ክልል የደረሡ ሰብሎችን በመሰብሰብ ህዝቡን እያገለገለ ነው
አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 2 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት በትግራይ ክልል የደረሡ ሰብሎችን በመሰብሰብ ህዝቡን በማገልገል ላይ ይገኛል።
በፅኑ ህዝባዊ መሰረት ላይ የተገነባውና ከምንም በላይ ሃገሩንና ህዝቦቿን የሚያስቀድመው የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት አባላት በትግራይ ክልል ከህዝቡ ጋር በመልሶ ግንባታና ልማት ስራዎች ላይ እየተሳተፉና እገዛ እያደረጉ ይገኛሉ።
ሰብል በደረሰባቸው አካባቢዎች ሰራዊቱ ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ሰብል በመሰብሰብ የህዝብ ልጅነቱን ዳግም እያስመሰከረ ነው።
በደቡብ አፍሪካ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የነፈሰው የሰላም አየር የክልሉ ህዝብ ወደ መደበኛ ኑሮው እንዲመለስ በር ከፍቶለታል።
የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከትግራይ ህዝብ ጋር በመሆን በግብርናና በሌሎች የመሰረተ ልማት መልሶ ግንባታ ስራዎችም በጋራ እየሰሩ ይገኛሉ።