በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ መስፍን አርአያ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ይቭጌኒ ተርኪን ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ መስፍን አርአያ ጋር ተወያዩ።
በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንዳስታወቀው፥ አምባሳደር ይቭጌኒ ተርኪን እና መስፍን አርአያ በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ የስራ እንቅስቃሴዎች ዙሪያ መክረዋል።
በተለይም በኢትዮጵያ መንግሥትና በህወሓት መካከል ዘላቂ የግጭት ማስወገድ ስምምነት መፈረሙን ተከትሎ ኮሚሽኑ በሚያደርገው አካታች ሀገራዊ ምክክር ዙሪያ መምከራቸውን ኤምባሲው ገልጿል።