Fana: At a Speed of Life!

ለሦስት ቀናት ክፍት ሆኖ የቆየው የማዕድንና ቴክኖሎጂ ዓለም ዓቀፍ ኤክስፖ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሕዳር 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ለህብረተሰቡ ክፍት ሆኖ የቆየው የማዕድንና ቴክኖሎጂ ዓለም ዓቀፍ ኤክስፖ ተጠናቀቀ፡፡

የኤክስፖው ዓላማ ኢትዮጵያ ያሏትን የማዕድን ሀብት እና ቴክኖሎጂዎች ለዓለም ለማስተዋወቅ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም በዘርፉ ላይ ያለውን የቴክኖሎጂ እና የዕውቀት ውስንነት ለመፍታት ብሎም የገበያ ትስስር ለማጠናከር ዓልሞ ለሦስት ቀናት ሲካሄድ ቆይቷል፡፡

በኤክስፖው የማዕድን አቅራቢዎች፣ አምራቾች፣የቴክኖሎጂ ውጤቶችን የያዙ ተቋማትና የዘርፉ አማካሪዎች ምርቶቻቸውን አስተዋውቀዋል።

በሥነ ስርዓቱ ላይ÷ በዘርፉ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን መፍታት በሚቻልበት ሁኔታ፣ በዘርፉ የተሰማሩ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ባለሀብቶች እንዲሁም ኩባንያዎች ያነሷቸው ጥያቄዎች ላይ ውይይት ተካሄዷል፡፡

ከውይይቱ ተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች የማዕድን ሚኒስትር ታከለ ኡማ ፣ የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሺዴ፣ የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሠፋ እንዲሁም የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በመራዖል ከድር

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.